ከኤኮኖሚው ዓለም

40 Episodes
Subscribe

By: DW

በሣምንታዊው የከኤኮኖሚው ዓለም መሰናዶ የኢትዮጵያ፣ አፍሪካ እና ዓለምን ምጣኔ ሐብታዊ ይዞታ የተመለከቱ ትንታኔዎች፣ ቃለ መጠይቆች እና ዘገባዎች ይቀርባሉ። ይኸ መሰናዶ ሀገራት የሚያወጧቸውን ኤኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች፣ መሪዎች የሚወስዷቸውን ምጣኔ ሐብታዊ ውሳኔዎች በመፈተሽ ጥቅም እና ጉዳታቸውን ያቀርባል።

✂️ Turn this podcast into clips
የኢትዮጵያ ብር የምንዛሪ ተመን ከዶላር አኳያ በዓመት 15 በመቶ ተዳክሟል
የኢትዮጵያ ብር የምንዛሪ ተመን ከዶላር አኳያ በዓመት 15 በመቶ ተዳክሟል episode artwork
08/05/2026

የኢትዮጵያ ብር ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ ከዶላር አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን 15 በመቶ ተዳክሟል። በሐምሌ 2016 ተግባራዊ የተደረገው የውጭ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት ለውጥ ወርቅና ቡናን የመሳሰሉ ሸቀጦችን የወጪ ንግድ እንዳበረታታ ቢታመንም ሸማቾችን በኃይል የጎዳ ነው። ከዚያ ባሻገር በመደበኛ እና ትይዩ የውጭ ምንዛሪ ገበያዎች መካከል ያለው የተመን ልዩነት አሁንም በሚጠበቀው ልክ አልጠበበም።


የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ኩባንያዎች በካፒታል ገበያ እንዲመዘግቡ ግፊት እያደረጉ ነው
የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ኩባንያዎች በካፒታል ገበያ እንዲመዘግቡ ግፊት እያደረጉ ነው episode artwork
07/29/2026

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ሥራ ከጀመረ ከ18 ወራት በኋላ ባለሥልጣናቱ ኩባንያዎች ድርሻዎቻቸውን እንዲያስመዘገቡ እየጎተጎቱ ነው። እስካሁን ስድስት ኩባንያዎች ድርሻዎቻቸውን በሁለተኛው ገበያ ያስመዘገቡ ሲሆን አምስቱ የግል ባንኮች ናቸው።


የባሕረ ሰላጤው ሃገራት አፍሪካ ውስጥ በቢሊዮን ዶላሮች መዋዕለ-ንዋይ የሚያፈሱት ለምንድነው?
የባሕረ ሰላጤው ሃገራት አፍሪካ ውስጥ በቢሊዮን ዶላሮች መዋዕለ-ንዋይ የሚያፈሱት ለምንድነው? episode artwork
07/22/2026

ሀብታሞቹ የባሕረ ሰላጤው ሃገራት በቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት መዋዕለ ንዋይ በአፍሪካ በማፍሰስ ላይ ናቸው። የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችና ሳዑዲ አረቢያን የመሳሰሉት ሃገራት የአፍሪካን ገበያ ሲያማትሩ ማሳካት የሚፈልጓቸው አላማዎች ግን የተለያዩ ናቸው። የዶይቸ ቬለው ኬርስተን ክኒፕ ያጠናቀረው ዘገባ ለባሕረ ሰላጤው ሃገራት መዋዕለ-ንዋይ መስፋፋት ገፊው ምክንያት ምንድነው? የአፍሪካ ሃገራትስ ምን ይጠቀማሉ? የሚለውን ይፈትሻል።


የኢትዮጵያ መንግሥት ባንኮች ከሚሰጡት ብድር የተወሰነው ለማምረቻ ዘርፍ እንዲመደብ የሚያስገድድ ሕግ እንዳያወጣ ተመከረ
የኢትዮጵያ መንግሥት ባንኮች ከሚሰጡት ብድር የተወሰነው ለማምረቻ ዘርፍ እንዲመደብ የሚያስገድድ ሕግ እንዳያወጣ ተመከረ episode artwork
07/15/2026

የኢትዮጵያ መንግሥት ባንኮች ከሚሰጡት ብድር የተወሰነውን ለማምረቻ ዘርፍ እንዲመድቡ የሚያስገድድ ሕግ ለማውጣት የያዘው ዕቅድ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ባለሙያዎች ተቃውሞ ገጥሞታል። በባንኮች ላይ ተጥሎ የቆየው የብድር ገደብ መነሳቱ ግን ባንኮች ለአምራቹ ዘርፍ የተሻለ ብድር እንዲሰጡ ዕድል እንደሚፈጥር የብሔራዊ ባንክ ገዢ ተናግረዋል። ባለፈው ሰኞ ይፋ በተደረገው ውሳኔ በ24 በመቶ ተገድቦ የነበረው የባንኮች ብድር ዕድገት ሙሉ በሙሉ የተነሳ ሲሆን የብሔራዊ ባንክ የወለድ ተመን ወደ 16% ከፍ ብሏል።


የግል ባንኮች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይውጣ ለተባለበት የወርቅ ግብይት ዝግጁ ናቸው?
የግል ባንኮች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ይውጣ ለተባለበት የወርቅ ግብይት ዝግጁ ናቸው? episode artwork
07/08/2026

ባለፈው ዓመት 3.4 ቢሊዮን ዶላር የነበረው የወርቅ የወጪ ንግድ ዘንድሮ 5.5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በብቸኝነት ከተቆጣጠረው ገበያ እንዲወጣ አይኤምኤፍ ግፊት እያደረገ ነው። የግል ባንኮች የወርቅ ግብይትን ለማካሔድ የሚያስችል የባለሙያ፣ የጥሬ ገንዘብ እና የመሠረተ-ልማት እጥረት አለባቸው።


የዐቢይ መንግሥት ለኢትዮጵያ ሕዝብ “መጥፎ” በተባለ ሥምምነት ወደ ንግድ ብድር ሊመለስ ነው?
የዐቢይ መንግሥት ለኢትዮጵያ ሕዝብ “መጥፎ” በተባለ ሥምምነት ወደ ንግድ ብድር ሊመለስ ነው? episode artwork
07/01/2026

ውድ ወለድ የሚከፈልባቸው የንግድ ብድሮች እንዳቆሙ በተደጋጋሚ ምለው የሚገዘቱት የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ቃላቸው የሚፈተንበት ሥምምነት ከቦንድ ባለቤቶች ጋር አድርገዋል። ሥምምነቱ ኢትዮጵያ እስከ 9% ወለድ የሚከፈልበት ቦንድ እንድታወጣ የሚያደርግ ነው። ኢትዮጵያ ቦንዱን ካላወጣች ለግል አበዳሪዎቿ እስከ 90 ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል ትገደዳለች።


“የኢትዮጵያ ዕዳ አሁን ዘላቂ ነው” የብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካልኝ
“የኢትዮጵያ ዕዳ አሁን ዘላቂ ነው” የብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካልኝ episode artwork
06/24/2026

የብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካልኝ የኢትዮጵያ የዕዳ ጫና “ዘላቂ” ወደሚባልነት ደረጃ ዝቅ እንዳለ ተናግረዋል። ዶክተር ኢዮብ የዕዳ ጫናው መቃለሉን የገለጹት ለአከፋፈል ሽግሽግ የሚካሔደው ድርድር ሳይጠናቀቅ ነው። በድርድሩ የሚፈጸሙ የሁለትዮሽ ሥምምነቶች ሲተገበሩ ኢትዮጵያ የሁለት ዓመት ዕዳ በአንድ በጀት ዓመት ልትከፍል እንደምትችል የገንዘብ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ አሕመድ ሽዴ ከፍተኛ አማካሪ ገልጸዋል።


ኢትዮጵያ በ2019 ነዳጅ ለመሸመት 6 ቢሊዮን ዶላር ታወጣለች ተብሎ ይጠበቃል
ኢትዮጵያ በ2019 ነዳጅ ለመሸመት 6 ቢሊዮን ዶላር ታወጣለች ተብሎ ይጠበቃል episode artwork
06/17/2026

የኢትዮጵያ መንግሥት በሚቀጥለው ዓመት ነዳጅ ለመሸመት 6 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ሊያደርግ እንደሚችል የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ ተናግረዋል። መንግሥት በዓመቱ በኤክሳይዝ ታክስ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከነዳጅ 235.6 ቢሊዮን ብር ገደማ መሰብሰብ ይፈልጋል። ለሚቀጥለው ዓመት የተዘጋጀው በጀት ለነዳጅ ድጎማ 20 ቢሊዮን ብር መታቀዱን አሳይቷል።


ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ ከፈቀደው ብድር 200 ሚሊዮን ዶላር አስቀድሞ ሊለቅ ነው
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ ከፈቀደው ብድር 200 ሚሊዮን ዶላር አስቀድሞ ሊለቅ ነው episode artwork
06/10/2026

አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን የገጠሙት ጦርነት ያሳደረውን ተጽዕኖ ኢትዮጵያ እንድትቋቋም አይኤምኤፍ (IMF) ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ከፈቀደው ብድር ውስጥ 200 ሚሊዮን ዶላር አስቀድሞ እንዲለቀቅ ታቅዷል። ገንዘቡ የተራዘመ ብድር አቅርቦት መርሐ-ግብር አምስተኛ ግምገማ ሲጸድቅ ከሚለቀቀው 468 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ የሚካተት ነው።


የሥራ እጥነት እና የመፍትሄ እርምጃዎች በኢትዮጵያ
የሥራ እጥነት እና የመፍትሄ እርምጃዎች በኢትዮጵያ episode artwork
06/03/2026

ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተመረቁ ወጣት ኢትዮጵያውያን ዲግሪ ይዘው ሥራ ማግኘት ቸግሯቸዋል። ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በኬሚካል ምህንድስና የተመረቀችው ወጣት ሥራ ሲጠፋ "ይኸን ሁሉ አመት ባላቃጠልኩ" ለማለት በቅታለች።


ኢትዮጵያ 60 ሚሊዮን ገደማ ዜጎቿ ኃይል ሳያገኙ ለጎረቤቶቿ ለምን ትሸጣለች?
ኢትዮጵያ 60 ሚሊዮን ገደማ ዜጎቿ ኃይል ሳያገኙ ለጎረቤቶቿ ለምን ትሸጣለች? episode artwork
05/20/2026

ታላቁን የህዳሴ ግድብ፣ የአሰላ እና የአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎችን በተከታታይ ያስመረቀችው ኢትዮጵያ ለኬንያ የምትሸጠውን ኤሌክትሪክ ለማሳደግ እያጤነች ትገኛለች። አራት ተማሪ ልጆቻቸው ትምህርታቸውን በኩራዝ የሚያጠኑትን እናት ጨምሮ 60 ሚሊዮን ገደማ ኢትዮጵያውያን ግን የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያገኙበትን ቀን ይናፍቃሉ።


ባይናንስ ከአርብ ጀምሮ በኢትዮጵያ ብር የሚደረግ ግብይት ያቆማል
ባይናንስ ከአርብ ጀምሮ በኢትዮጵያ ብር የሚደረግ ግብይት ያቆማል episode artwork
05/13/2026

በዓለም ትልቁ የክሪፕቶከረንሲ መገበያያ የሆነው ባይናንስ ከመጪው አርብ ጀምሮ በብር የሚደረጉ ግብይቶች እንደሚያቆም አስታውቋል። ባይናንስ በዘረጋው የመገበያያ መድረክ ከኢትዮጵያ የሚሳተፉት ክሪፕቶከረንሲ “አዋጭ ኢንቨስትመንት” እንደሆነ የሚያምኑ ወጣቶች ናቸው። መሰል ግብይቶች ግን ለሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ተመራጭ እየሆኑ መጥተዋል።


የኢትዮጵያ መንግሥት የስድስት ወራት የሀገር ውስጥ ብድር ወለድ ክፍያ ካለፈው ዓመት ሲነጻጸር 250% ጨመረ
የኢትዮጵያ መንግሥት የስድስት ወራት የሀገር ውስጥ ብድር ወለድ ክፍያ ካለፈው ዓመት ሲነጻጸር 250% ጨመረ episode artwork
05/06/2026

የኢትዮጵያ መንግሥት የ2018 የመጀመሪያ መንፈቅ የሀገር ውስጥ ብድር ወለድ ክፍያ 126.5 ቢሊዮን ብር መድረሱን የገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው ሰነድ አሳይቷል። የወለድ ክፍያው በስድስት ወራት ለዕዳ ከተመደበው በጀት 64.6% ድርሻ አለው። ካለፈው ዓመት ተመሣሣይ ወቅት አኳያ ሲነጻጸር ግን ከ250 በመቶ በላይ ጨምሯል። በ2017 የመጀመሪያ ስድስት ወራት ለሀገር ውስጥ ወለድ መንግሥት 36 ቢሊዮን ብር ከፍሎ ነበር።


የአውሮፓ ኅብረት የበጀት ድጋፍን ጨምሮ ለኢትዮጵያ 559 ሚሊዮን ዩሮ ለማቅረብ ቃል ገባ
የአውሮፓ ኅብረት የበጀት ድጋፍን ጨምሮ ለኢትዮጵያ 559 ሚሊዮን ዩሮ ለማቅረብ ቃል ገባ episode artwork
04/22/2026

የአውሮፓ ኅብረት በትግራይ ጦርነት ምክንያት ያቋረጠውን የበጀት ድጋፍ ወደ 140 ሚሊዮን ዩሮ ከፍ አድርጎ እንደሚጀምር አስታውቋል። ለዲጂታል ኢኮኖሚ 150 ሚሊዮን ዩሮ፤ ኤሌክትሪክ ለማስፋፋት፣ ፋይበር ኦፕቲክ ለመዘርጋትና የአሸጎዳ የንፋስ ኃይል ማመንጫን ለመጠገን 269 ሚሊዮን ዩሮ ያቀርባል። የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ 130 ሚሊዮን ዩሮ ለዘመን ባንክ እና ለኢትዮጵያ መንግሥት ለማበደር ሥምምነት ተፈራርሟል።


በአየር ንብረት ለውጥ የኢትዮጵያ ቡና አብቃይ አካባቢዎች ሲስፋፉ በኮሎምቢያ እና ሖንዱራስ እንደሚቀንስ ጥናት አሳየ
በአየር ንብረት ለውጥ የኢትዮጵያ ቡና አብቃይ አካባቢዎች ሲስፋፉ በኮሎምቢያ እና ሖንዱራስ እንደሚቀንስ ጥናት አሳየ episode artwork
04/15/2026

የአየር ንብረት ለውጥ በኢትዮጵያ ለአረቢካ ቡና በጣም ምቹ የሆነውን አካባቢ አሁን ከሚገኝበት 38% በመቶ በምዕተ-ዓመቱ አጋማሽ ወደ 49% ከፍ ሊያደርገው እንደሚችል አንድ ጥናት አሳይቷል። በሮቦ ባንክ ጥናት መሠረት የዓለም ሙቀት ሲጨምር በኢትዮጵያ ደጋማ አካቢዎችን ቡና አምራች ሊያደርጋቸው ቢችልም ኮሎምቢያ እና ሖንዱራስ ተጎጂ ናቸው። ደጋማ አካባቢዎች ሞቃታማ እየሆኑ ሲሔዱ በቡና አመቺነታቸው ቢጨምርም የዝቅተኛ ወይም ቆላማ አካባቢዎች በአንጻሩ ይቀንሳል።


የኢትዮጵያ መንግሥት “ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ” የሚከላከል ደንብ እንዲያወጣ እና የግብር እፎይታ እንዲሰጥ ተጠየቀ
የኢትዮጵያ መንግሥት “ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ” የሚከላከል ደንብ እንዲያወጣ እና የግብር እፎይታ እንዲሰጥ ተጠየቀ episode artwork
04/08/2026

አምስት ሊትር ዘይት በአሶሳ፣ ደሴ እና መቐለ ከተሞች ከ2,200 እስከ 2,500 ብር እየተሸጠ ነው። የመንግሥት መዋቅሮች የዋጋ ጭማሪዎችን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ ነው። የኢትዮጵያ ሸማቾች መብቶች ተቆርቋሪ ድርጅት “ያልተገቡ የዋጋ ጭማሪዎችን በግልጽ የሚከለክል እና የሚያስቀጣ ልዩ መመሪያ” መንግሥት በአስቸኳይ እንዲያወጣ ጥሪ አቅርቧል።


የኢራን ጦርነት በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ላይ “አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ይጠበቃል”
የኢራን ጦርነት በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ላይ “አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ይጠበቃል” episode artwork
04/01/2026

በኢትዮጵያ የነጭ ናፍጣ አቅርቦት በአማካይ በቀን ከ9.2 ሚሊዮን ሊትር ወደ 4.5 ሚሊየን ሊትር ቀንሷል። ሀገሪቱ የኢራን ጦርነት ሲቀሰቀስ የገዛችውን 180,000 ሜትሪክ ቶን ነዳጅ ማስገባት አልቻለችም። በወር ከ15 እስከ 20 ቢሊዮን ብር ለነዳጅ ለመደጎም መገደዱን የገለጸው መንግሥት ዜጎች “ቅድሚያ የማይሰጣቸው ጉዞዎች እንዲሰርዙ” መክሯል። የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ የኢራን ጦርነት ያስከተለውን የነዳጅ ቀውስ ለመቋቋም ኢትዮጵያውያን “ቅድሚያ የማይሰጣቸው ጉዞዎች እንዲሰርዙ” መክረዋል።


በአማራ ክልል ያለው የነዳጅ ዘይት እጥረትና ድብቅ ገበያ
በአማራ ክልል ያለው የነዳጅ ዘይት እጥረትና ድብቅ ገበያ episode artwork
03/25/2026

ነዳጅ ከማደያዎች ውጪ በሊትር ደሴ 350 ብር፣ ኮምቦልቻ 500 ብር ዳባት 900 ብር መሸጡን አሽከርካሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በጎንደር እና ባሕር ዳር በነዳጅ ማደያዎች ለወረፋ ከ2,000 እስከ 10,000 ብር ይከፈላል። በአማራ ክልል የነዳጅ እጥረት እና የዋጋ ለውጥ በግብርና እና በኢንዱስትሪ ምርቶች መሸጫ ላይ ጭማሪ አስከትሏል።


የነዳጅ ዋጋ ጨምሮ የቡና ሲቀንስ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ብርቱ ፈተና ከፊቱ ተጋርጦበታል
የነዳጅ ዋጋ ጨምሮ የቡና ሲቀንስ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ብርቱ ፈተና ከፊቱ ተጋርጦበታል episode artwork
03/18/2026

በታኅሳስ፣ ጥር እና የካቲት ወራት በኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት ነጠላ አሀዝ ሆኖ የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት የነዳጅ ዋጋ ሲያሻቅብ ሊባባስ ይችላል። የነዳጅ ዋጋ የናረው ሀገሪቱ በቡና ንግድ በዓለም አቀፍ ገበያ የተጋረጠባትን ፈተና ለመሻገር በምትሞክርበት ወቅት መሆኑ በባለሥልጣናቱ ዘንድ ሌላ ሥጋት የፈጠረ ጉዳይ ነው።


የነዳጅ ዋጋ “አስፈሪ በሆነ መልኩ” ሲንር ኢትዮጵያ “የቁጠባ እርምጃዎች” ልትከተል ነው
የነዳጅ ዋጋ “አስፈሪ በሆነ መልኩ” ሲንር ኢትዮጵያ “የቁጠባ እርምጃዎች” ልትከተል ነው episode artwork
03/11/2026

አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን በገጠሙት ጦርነት የነዳጅ ዋጋ ሲንር የኢትዮጵያ መንግሥት ለቤንዚን እና ለነጭ ናፍጣ በሊትር የሚያደርገው ድጎማ በ44 ብር ገደማ እንደጨመረ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሽዴ ተናግረዋል። ከነዳጅ በተጨማሪ የማዳበሪያ ዋጋ በዓለም ገበያ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በማሳየቱ የኢትዮጵያ ገበሬዎችን ሊፈታተን ይችላል። ጦርነቱ ከመቀስቀሱ በፊት የ50 ኪሎግራም የዩሪያ ከረጢት በኢትዮጵያ ከ12 እስከ 15 ዶላር ይሸጥ ነበር። በዓለም አቀፍ ገበያ የ30% የዋጋ ጭማሪ ሲከሰት በኢትዮጵያ ያለው የችርቻሮ ዋጋ ከ16 እስከ 20 ዶላር ከፍ ይላል ተብሎ እንደሚገመት የቢዝነስ ደቨሎፕመንት ባለሙያው ኢዶሳ ታመነ ይናገራሉ።


እስራኤል እና አሜሪካ ከኢራን የገጠሙት ጦርነት በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር አደረገ
እስራኤል እና አሜሪካ ከኢራን የገጠሙት ጦርነት በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር አደረገ episode artwork
03/04/2026

በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ እስራኤል እና አሜሪካ ከኢራን ጦርነት ከመግጠማቸው በፊት ከነበረው ዋጋ 12% ገደማ ጨምሮ 82 ዶላር አካባቢ ደርሷል። በቀጠር እና ሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ነዳጅ ማምረቻዎች፤ በሖርሙዝ ወሽመጥ የሚቀዝፉ መርከቦች ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል። በሖርሙዝ የመርከቦች ምልልስ በ80% ቀንሷል፤ ወደ 3,200 የሚሆኑ መርከቦች ሥራ ፈተዋል


ለኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ የአጋርነት መዋጮ መሰብሰብ ተጀምሯል
ለኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ የአጋርነት መዋጮ መሰብሰብ ተጀምሯል episode artwork
02/25/2026

ለኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ የባንክና ቴሌኮም አገልግሎቶችን ጨምሮ በተለያዩ ስልቶች የአጋርነት መዋጮ መሰብሰብ ተጀምሯል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኝ ተቋም ባልደረባ ባለፈው ወር ከደመወዛቸው 0.5% መቆረጡን ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል። ባለሙያዎች እንደ አሜሪካ ያሉ ሀገራት የሚሰጡት ርዳታ በመቀነሱ አደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ እንደሚያስፈልግ ቢስማሙም መዋጮው ጫና እንደሚኖረው ተናግረዋል።


በኢትዮጵያ ጦርነት ዳግም ሲያንዣብብ የትግራይ ክልል ነዋሪዎችና ኢኮኖሚ ካሁኑ ዳፋው ተጭኗቸዋል
በኢትዮጵያ ጦርነት ዳግም ሲያንዣብብ የትግራይ ክልል ነዋሪዎችና ኢኮኖሚ ካሁኑ ዳፋው ተጭኗቸዋል episode artwork
02/18/2026

በኢትዮጵያ ሌላ ጦርነት ሲያዣብብ በትግራይ ክልል የነዳጅ ምርቶች፣ ጤፍ እና ዘይትን ጨምሮ የምግብ ግብዓቶች በአንድ ሣምንት የዋጋ ጭማሪ ታይቶባቸዋል። በክልሉ ከኤቲኤም ገንዘብ ማግኘት አይቻልም። ባንኮች ደንበኞቻቸው ወጪ የሚያደርጉትን የገንዘብ መጠን ገድበዋል። በክልሉ በተፈጠረ ከፍተኛ የጥሬ ገንዘብ እጥረት ምክንያት ለንግድ እና አገልግሎቶች ክፍያ የሚፈጸመው በሞባይል የገንዘብ ማዘዋወሪያዎች ሆኗል።


“ማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እያመጣን ትርፋማ መሆን እንችላለን” የላቭግራስ ኢትዮጵያ መሥራች ዮናስ አድማሱ
“ማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እያመጣን ትርፋማ መሆን እንችላለን” የላቭግራስ ኢትዮጵያ መሥራች ዮናስ አድማሱ episode artwork
02/11/2026

የብሪታኒያ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት (BII) ለላቭግራስ ኢትዮጵያ የአምስት ሚሊዮን ዶላር ፋይናንስ እንደሚያቀርብ አስታውቋል። ኩባንያው በሱሉልታ በሚገኘው ፋብሪካ ከጤፍ ፓስታ እና ኩኪሶችን ጨምሮ የተለያዩ ምግቦች እያመረተ ለዓለም ገበያ የሚያቀርብ ነው። ላቭግራስ ብድሩን ያገኘው “ማኅበረሰቡ ላይ አዎንታዊ ለውጥ እያመጣን ትርፋማ መሆን እንችላለን” የሚል ግልጽ ዓላማ ስላለው እንደሆነ ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ ዮናስ አድማሱ ይናገራሉ። ዮናስ ኩባንያውን ከመመሥረታቸው በፊት በቢኤንፒ ፓሪባ፣ ጄፔ ሞርጋን እና ክሬዲት ስዊዝ ባንኮች ሠርተዋል።


የግል አበዳሪዎች ኢትዮጵያን ሊከሱ እንደሚችሉ ቢገልጹም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአከፋፈል ሽግሽግ ይጠብቃሉ
የግል አበዳሪዎች ኢትዮጵያን ሊከሱ እንደሚችሉ ቢገልጹም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአከፋፈል ሽግሽግ ይጠብቃሉ episode artwork
02/04/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያን ዕዳ ለማሸጋሸግ በሚደረገው ጥረት “በሁለት ዓመት ይከፈል የነበረው ዕዳ እንደየአበዳሪው ሁኔታ እስከ 15 ዓመት እንዲራዘም ሥምምነት” መፈጸሙን ተናግረዋል። የግል አበዳሪዎች ግን ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ያደረጉት ሥምምነት ውድቅ ከሆነ በኋላ በእንግሊዝ ፍርድ ቤት ክስ ሊመሠርቱ እንደሚችሉ ገልጸዋል። ገንዘብ ሚኒስቴር እና የግል አበዳሪዎች በመርኅ ደረጃ ያደረጉት ሥምምነት ተግባራዊ ቢሆን ኖሮ “የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዙ እንዲከፍል በማስገደድ አስፈላጊ የመንግሥት አገልግሎቶችን አደጋ ላይ ይጥላል” የሚሉት የዴብት ጀስቲስ ዋና ዳይሬክተር ሐይዲ ቻው ውድቅ መደረጉን ደግፈዋል።


በጨረታ ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ያከፋፈለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በካፒታል ገበያ በኩል የባንኮች የውጭ ምንዛሪ መገበያያ ሥራ አስጀመረ
በጨረታ ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ያከፋፈለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በካፒታል ገበያ በኩል የባንኮች የውጭ ምንዛሪ መገበያያ ሥራ አስጀመረ episode artwork
01/28/2026

በጨረታ 500 ሚሊዮን ዶላር ያከፋፈለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX) በኩል ባንኮች የውጭ ምንዛሪ የሚገበያዩበት ሥርዓት አስጀምሯል። ባንኮች በመጫረቻ ዋጋ የጠየቁት 592.3 ሚሊዮን ዶላር ከቀረበው በላይ ነበር። ከ31 ባንኮች ለ25ቱ የተከፋፈለው ዶላር መጠን ከፍተኛ ቢሆንም በምንዛሪ ተመን ላይ ትልቅ ለውጥ አላመጣም።


የድህረ ምርት ብክነትና በምግብ ዋስትና ላይ ያለው ተፅዕኖ
የድህረ ምርት ብክነትና በምግብ ዋስትና ላይ ያለው ተፅዕኖ episode artwork
01/21/2026


ከኤኮኖሚዉ ዓለም፣ የግዙፉ አዉሮፕላን ማረፊያ ግንባታና ፈተናዎቹ
ከኤኮኖሚዉ ዓለም፣ የግዙፉ አዉሮፕላን ማረፊያ ግንባታና ፈተናዎቹ episode artwork
01/14/2026

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንደሚሉት በ3 ሺህ 900 ሄክታር ቦታ ላይ የሚያርፈው አዲሱ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ በሙሉ አቅሙ ሲጠናቀቅ 110 ሚሊየን ደንበኞችን በዓመት የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል


ጀርመን ለኢትዮጵያ በምትሰጠው ድጋፍ ለጸጥታ ጉዳዮች ትኩረት እየሰጠች ነው?
ጀርመን ለኢትዮጵያ በምትሰጠው ድጋፍ ለጸጥታ ጉዳዮች ትኩረት እየሰጠች ነው? episode artwork
12/17/2025

ኢትዮጵያ እና ጀርመን ባለፈው ሣምንት 100 ሚሊዮን ዩሮ ቀጥተኛ የበጀት ድጋፍን ጨምሮ ለሦስት ዓመታት የሚዘልቅ “የትብብር ማዕቀፍ ሥምምነት” ተፈራርመዋል። በሥምምነቱ ጀርመን ለኢትዮጵያ 206 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብታለች።


በኢትዮጵያ ምርጫ ሲቃረብ ገዥው ብልጽግና ፓርቲ ወደ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች እያደላ ነው
በኢትዮጵያ ምርጫ ሲቃረብ ገዥው ብልጽግና ፓርቲ ወደ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች እያደላ ነው episode artwork
12/10/2025

የኢትዮጵያ ሰባተኛ ምርጫ በመካሔድ ላይ የሚገኙ ግጭቶች፣ የፖለቲካ ምኅዳር መጥበብ እና የተቃዋሚዎች መዳከም አጥሎበታል። ገዥው ብልጽግና ፓርቲ እንደ ስኬት የሚቆጥራቸውን ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች አጉልቶ ለማቅረብ ሲጥር ይታያል። የኑሮ ውድነት፣ ሥራ አጥነት እና የድሕነት መጨመርን የመሳሰሉ አንገብጋቢ ጉዳዮች ክርክር ሊደረግባቸው የሚገባ ጉዳዮች ናቸው።


የካፒታል ገበያ አገልግሎት አቅራቢዎች “እባካችሁ በተሰጣችሁ ፈቃዶች ላይ አትተኙባቸው”
የካፒታል ገበያ አገልግሎት አቅራቢዎች “እባካችሁ በተሰጣችሁ ፈቃዶች ላይ አትተኙባቸው” episode artwork
12/03/2025


የኢትዮጵያ እና የጀርመን ቢዝነስ ፎረም በበርሊን ተካሔደ
የኢትዮጵያ እና የጀርመን ቢዝነስ ፎረም በበርሊን ተካሔደ episode artwork
11/26/2025

የኢትዮጵያ እና የጀርመን ኩባንያዎችን ከመንግሥት ባለሥልጣናት እና ከልማት ድርጅቶች የሚያገናኘው የቢዝነስ ፎረም በበርሊን ተካሒዷል። መርሐ-ግብሩ በታዳሽ ኃይል፣ በግብርና ውጤቶች ማቀነባበሪያ እና በዲጂታላይዜሽን ዘርፎች የተሰማሩ ኩባንያዎች የተጋበዙበት ነው።


የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አምስት ተጨማሪ ኩባንያዎች እያቋቋመ ነው
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አምስት ተጨማሪ ኩባንያዎች እያቋቋመ ነው episode artwork
11/19/2025

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የመማሪያ መጻሕፍት አታሚ ድርጅት እና የወጣቶች የኢንቨስትመንት ባንክ ጨምሮ በዚህ ዓመት አምስት ኩባንያዎች እንደሚያቋቁም አሳውቋል። ከሁለት የሩሲያ ኩባንያዎች ጋር የመግባቢያ ሥምምነቶች የተፈራረመው ተቋም ከ2011 ጀምሮ የስኳር ፋብሪካዎች ለመሸጥ ሲደረግ የነበረው ጥረት አቋርጧል።


በሰኔ ይጠናቀቃል የተባለው የመገጭ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ወጪ ስንት ነው?
በሰኔ ይጠናቀቃል የተባለው የመገጭ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ወጪ ስንት ነው? episode artwork
11/12/2025

በ2.5 ቢሊዮን ብር የመነሻ ዋጋ ተጀመረው የመገጭ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት በጀት 20.7 ቢሊዮን ብር መድረሱን የፌድራል ሥነ-ምግባር እና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ሰነድ አሳይቷል። ለግንባታው በ2018 በጀት ውስጥ ከ4.9 ቢሊዮን ብር በላይ ተመድቧል። መንግሥት 13 ዓመታት የተጓተተው ግንባታ በስምንት ወራት እንደሚጠናቀቅ ገልጿል።


የኢትዮጵያ ክልሎች እና ከተሞች የማዘጋጃ ቤት ቦንድ ቢያወጡ ማን ያበድራቸዋል?
የኢትዮጵያ ክልሎች እና ከተሞች የማዘጋጃ ቤት ቦንድ ቢያወጡ ማን ያበድራቸዋል? episode artwork
11/05/2025

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በቅርቡ ይፋ ባደረገው ሰነድ የክልል መንግሥታት እና የከተማ መስተዳድሮች ቦንድ በማውጣት ከገበያው የሚበደሩበት ሥርዓት የመዘርጋት ፍላጎት እንዳለው ፍንጭ ሰጥቷል። የማዘጋጃ ቤት ወይም የከተማ አስተዳደር ቦንዶች ለመሠረተ-ልማት ግንባታ የሚያስፈልግ ገንዘብ ለመበደር የሚያገለግሉ ናቸው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የሲዳማ ክልል በቁልፍ የልማት ዘርፎች ረገድ ያለባቸውን የገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ ቦንድ በማውጣት ከገበያው የመበደር ፍላጎት እንዳላቸው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በቅርቡ ይፋ ያደረገው አንድ ጥናት አሳይቷል።


የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዳሉት “ከ23 ቢሊዮን ዶላር አይበልጥም”?
የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዳሉት “ከ23 ቢሊዮን ዶላር አይበልጥም”? episode artwork
10/29/2025

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ ከ23 ቢሊዮን ዶላር እንደማይበልጥ ተናግረዋል። የዓለም ባንክ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የዕዳ ዘላቂነት ትንተና በአንጻሩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የተበደሩትን ጨምሮ የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ 31.7 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ ያሳያል።


የዶላር ምንዛሪ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንድ ሣምንት ብቻ ከአምስት ብር በላይ ጨመረ
የዶላር ምንዛሪ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንድ ሣምንት ብቻ ከአምስት ብር በላይ ጨመረ episode artwork
10/22/2025

ባለፈው አንድ ሣምንት ንግድ ባንክ ዶላር የሚገዛበት እና የሚሸጥበት ተመን አምስት ብር ከ50 ሳንቲም ገደማ ከፍ ብሏል። የብሔራዊ ባንክ አመልካች ዕለታዊ የምንዛሪ ተመን በአንጻሩ 150 ብር ከ90 ሳንቲም ደርሷል። ብር በውጭ ምንዛሪ ገበያው መዳከሙን ሲቀጥል ብሔራዊ ባንክ እርምጃ ለመውሰድ በድጋሚ ዝቷል።


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስር የውጪ ምንዛሪ ጨረታዎች ምን አሳኩ?
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስር የውጪ ምንዛሪ ጨረታዎች ምን አሳኩ? episode artwork
10/15/2025

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሪ ግብይት ሥርዓት ለውጥ ከተደረገ ወዲህ ባካሔዳቸው ጨረታዎች ከ690 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለባንኮች አከፋፍሏል። ጨረታዎቹ በትይዩ ገበያ ላይ እርምጃ ሲወሰድ የውጪ ምንዛሪ ገበያውን ማረጋጋት ቢችሉም ዋንኛ ዓላማቸውን ያሳኩ አይመስልም። በመደበኛ እና ትይዩ ገበያዎች የምንዛሪ ተመን ሲጨምር ልዩነታቸው አልጠበበም።


የኢትዮጵያ የኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ ልማት ፕሮጀክት እንደ ቀደሙት ሙከራዎች ያሰጋል?
የኢትዮጵያ የኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ ልማት ፕሮጀክት እንደ ቀደሙት ሙከራዎች ያሰጋል? episode artwork
10/08/2025

የኢትዮጵያ መንግሥት በሶማሌ ክልል ያስጀመረውን የነዳጅ ልማት ፕሮጀክት የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር አንድ አንጃ ተቃውሟል። ኦብነግ ፕሮጀክቱ “ምክክር” እንዳልተደረገበት እና ሕዝቡ “ፈቃዱን እንዳልሰጠ” ተችቷል። ከዚህ ቀደም በነዳጅ ፍለጋ ወቅት ከባድ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መፈጸማቸውን የሚያስታውሱ ተመራማሪዎች አዲሱ ፕሮጀክት “ጥንቃቄ” እንደሚሻ ይመክራሉ።


ኢትዮጵያ ለቢሊዮን ዶላር ዕዳ ሽግሽግ ከቦንድ ባለቤቶች ጋር የሚደረገውን ውይይት ውጤት እየጠበቀች ነው
ኢትዮጵያ ለቢሊዮን ዶላር ዕዳ ሽግሽግ ከቦንድ ባለቤቶች ጋር የሚደረገውን ውይይት ውጤት እየጠበቀች ነው episode artwork
10/01/2025

ኢትዮጵያ ከ10 ዓመታት በፊት ከግል ባለወረቶች አንድ ቢሊዮን ዶላር የተበደረችበት ቦንድ ባለቤቶች እና የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ፓሪስ ዉስጥ ውይይት ጀምረዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከግል አበዳሪዎቹ ጋር የሚደረገውን ድርድር ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የተራዘመ የብድር አቅርቦት አራተኛ ግምገማ በፊት የማጠናቀቅ ዕቅድ አለው።