ማሕደረ ዜና

40 Episodes
Subscribe

By: DW

ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘወትር ሰኞ ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሐገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀርብበታል። አዘጋጅ፣ ነጋሽ መሐመድ

ሶሪያ፤ አንድ አመት ክበሺር አላሳድ በኋላ
Today at 5:35 PM


የደቡብ አፍሪካ እና አሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ፍጥጫ ያየለበት የቡድን 20 ጉባኤ
11/24/2025

የቡድን 20 ጉባኤ ሲጠናቀቅ በሱዳን፣ ኮንጎ፣ በእስራኤል በጉልበት በተያዙት የፍልስጤም ግዛቶችና በዩክሬን “ፍትኃዊ፣ ሁሉን አቀፍና ዘላቂ ሰላም” እንዲወርድ እንደሚሠሩ መሪዎቹ ቃል ገብተዋል። በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሔደው ጉባኤ የደቡብ አፍሪካ እና የአሜሪካ ውዝግብ ተጭኖታል። ጉባኤው ሲጠናቀቅ አሜሪካ ቀጣይ ፕሬዝደንትነቱን አልተረከበችም።


ማሕደረ ዜና፣ የትራምፕ ተቃራኒ የአፍሪቃ መርሕ
11/17/2025

አንዳዶቹ ፎቶ ግራፎች ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዉስጥ የተነሱ መሆናቸዉ ቢረጋገጥም የነጮችን የበላይነት ለማስከበር ቆርጠዉ የተነሱት ዶናልድ ትራምፕ ግን ነጭ ደቡብ አፍሪቃዉያን ወደ አሜሪካ እንዲሰደዱ ፈቀደዋል።አሜሪካ ጥግ የምትገኘዉን የጃማይካ ስደተኛን ሳይቀር ከአሜሪካ ወደ አፍሪቃ ያስግዛሉ።መሰደድ የማይፈልጉትን የደቡብ አፍሪቃ ነጭ ዜጎችን ወደ አሜሪካ ይጋብዛሉ።ከአፍሪቃ ጋር የንግድ ግንኙነትን ማጠናቀር እሻለሁ ይላሉ፤ ደቡብ አፍሪቃን በዘረኝነት ያወግዛሉ።


ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ-ኤርትራ ምድር ሌላ ጦርነት እየተደገሰለት ይሆን?
11/10/2025

ኢትዮጵያ በየሥፍራዉ ከሚደረጉ ግጭቶች በተጨማሪ የኑሮ ዉድነት፣ ሰዎች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ደሕንነት እጦት፣ እገታና ግድያን የመሳሰሉ የሕግና ሥርዓት መጓደሎች አቃርጠዉ እንደያዟት ነዉ።ትግራይን ጨምሮ ከአራት ሚሊዮን የሚበልጥ ተፈናቃይ በየመጠለያ ጣቢያዉ እንደሰፈረ ነዉ።የኤርትራ ሁኔታም ከኢትዮጵያ የባሰ እንጂ ያነሰ አይደለም።በዚሕ ላይ አካባቢዉ ሌላ ጦርነት ይችል ይሆን?


የማክሰኞ ጥቅምት 25 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና
11/04/2025

ፓሪስ፥የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ያስተዋወቀ መድረክ ተከናወነ፣ ዴንሐግ፥ በሰዎች ማዘዋወር የተጠረጠረ ኤርትራዊ ላይ ኔዘርላንድስ ውስጥ ክስ ተከፈተ፣ ካርቱም፥ የሱዳን ተፋላሚ ኃይላት ለዕርቅ አወንታዊ ምላሽ መስጠታቸውን የትራምፕ ረዳት ተናገሩ፣ ዳርኤሰላም፥ ፖሊስ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚዎች የሚረብሹ ምስሎች እንዳይጋሩ አስጠነቀቀ፣ ቤርሊን፥ ጀርመን በሚቀጥለው የጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2026 ለዩክሬይን የምትሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ለማሳደግ ወሰነች


ማሕደረ ዜና፣ ኤል ፋሻር-የሱዳን እልቂት አዲስ ምዕራፍ
11/03/2025

የካይሮና የአቡዳቢ ገዢዎች የመንንን ለመደብደብ ጥብቅ ወዳጅ ነበሩ።ቀጠር በማዕቀብ ለመቅጣት ተባባሪ ነበሩ።የቀድሞዉን የሶሪያ መሪ በሽር አል አሰድን ለማስወገድ ተመሳጣሪ ነበሩ።ሱዳንና ሊቢያ ጦርነት ላይ ተቃራኒ ኃይላትን ይደግፋሉ።ሱዳንም የቀድሞ ወዳጆች የገጠሙት-ወዳጆችን ያቃረነ ጦርነት ማዕከል እንደሆነች ቀጥላለች።


ማሕደረ ዜና፣ የASEAN ጉባኤ፣ የትራምፕ ጉብኝትና የሲኖ-አሜሪካ ድርድር
10/27/2025

ቤጂንጎች ሲያመሩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ «የንግድ ጦርነት ቀላል ነዉ አልኩ እንጂ---ከቻይና ጋር ማለቴ አልነበረም» ማለታቸዉ ተዘገበ።ዘ-ኤኮኖሚስት የተሰኘዉ መፅሔት ደግሞ በቀደም «ቻይና በትራምፕ ዱላ አሜሪካናንን ደበደበች» አለ።የሁለቱ ሐገራት የንግድና የኤኮኖሚ ባለሥልጣናት ሰሞኑን ለ5ኛ ዙር እየተደ,ራደሩ ነዉ።የቻይና ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ጉዮ ጂያኩን ዛሬ እንዳሉት ዉይይቱ የሰከነና መግባባት የታየበት ነዉ።


ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ፣ ሶማሊያና ሶማሊላንድ ጥልፍልፍ
10/20/2025

የኢሮ ጉብኝት ባለፈዉ ሐሙስ ሲጠናቀቅ የበርበራ ወደብን የሚገነባዉ፣ DP ወርልድ የተባለዉ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ኩባንያ፣ መርከቦች ከርበራ ወደብ ጀበል ዓሊ ወደተባለዉ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ወደብ እና በተቃራኒዉ መጓዝ መጀመራቸዉን አስታዉቋል። በኢትዮጵያ-ሶማሊያና ሶማሊላንድ መሪዎች ጉብኝት፣ ዉይይት፣ የፖለቲካ ጥልፍልፉ የአቡዳቢና የካይሮ ገዢዎች በቀጥታም በተዘዋዋሪም ጫና ማድረጋቸዉ የተሠወረ አይደለም።ይሁንና የሶማሊላንድ ዲፕሎማቶች በግል እንዳሉት ኢሮ የመሩት የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ በኩል የቀረበለትን የሶማሊያ ፕሬዝደንትን ሥልት አልተቀበለዉም።ጉብኝቱም ባጭሩ ተጠናቅቋል።ምናልባት እስከሚቀጥለዉ ጊዜ።


ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የህወሓት የቃላት ጦርነት ንሯል።ይዋጉ ይሆን?
10/13/2025

ኢትዮጵያ ዘንድሮ የሕዳሴ ግድብን አስመርቃለች።፣የካሉብ ጋዝ ማምረቻና የማደባሪያ ፋብሪካን የመሠረት ድንጋይ ጥላለች።አማራ ክልል ከፋኖ፣ ኦሮሚያ ክልል ከኦነሠ ወይም OLA ጋር የሚደረገዉ ዉጊያ አሸናፊና ተሸናፊ ሳይለይበት እንደቀጠለ ነዉ።የኢትዮጵያ ምናልባትም የኤርትራ ክረምት ግን አብቅቷል።ዓየሩ ለወታደራዊ ንቅናቄ ይመቻል።እና ይዋጉ ይሆን?


ማሕደረ ዜና፣ የእስራኤል መጠቃት፣ የጋዛ ጦርነትና ድርድር 2ኛ ዓመት
10/06/2025

ሕዝባቸዉ በየአደባባዩ የሚያደርገዉ ግፊት የጠናባቸዉ የምዕራብ አዉሮጳ መሪዎች እየተግተለተሉ ለፍልስጤሞች የመንግሥትነት እዉቅና ሰጡ።ኔታንያሁ በሚጭሩት ጦርነት ዘለዉ በመግባት ወይም ለኔታንያሁ መንግስት ፍፁም ድጋፍ በመስጠታቸዉ ምክንያት አረብ-ሙስሊም እየራቃቸዉ፣ ሕዝብ እየተከፋባቸዉ፣ ከተቀረዉ ዓለምም እየተነጠሉ የመጡት ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጥብቅ ወዳጃቸዉን ኔታንያሁን በቅርቡ «በቃሕ» አሉሏቸዉ።ወይም ያሉ መሰሉ።


ማሕደረ ዜና፣ ዓለም መሪዎች እየተግባቡ ይሆን ወይስ ግራ እያጋቡ
09/29/2025

ሰዉዬዉ ከመቸኮላቸዉ የተነሰ በእስራኤል ላይ የሚለዉን በኢራን ላይ የተቃጣ አደጋ ብለዉት ነበር።ቸኩለዉ አሉት።ፈጥነዉ አረሙት።ኔታንያሁ እስራኤል ከመጥፋት አደጋ፣ ዓለምም ከመገደል ሥጋት ድኗል ቢሉም የለንድን፣ የፓሪስና የበርሊን መሪዎች አልተቀበሉትም። እንደ አሜሪካ ሁሉ የእስራኤል የቅርብ ወዳጆች፣ የኢራን ጠላቶች ፈረንሳይ፣ ብሪታንያና ጀርመን የኢራን የኑክሌር መርሐ-ግብር ያሰደረዉ ሥጋት አልተወገደም ይላሉ።ወይም የኔታንያሁን ማረጋገጪያ አላመኑትም።በሶስቱ ሐገራት ግፊት የተሰየመዉ የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት በኢራን ላይ ዳግም ዓለም አቀፍ ማዕቀብ እንዲጣል ወስኗል።


ማሕደረ ዜና፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የ80 ዓመት አዛዉንት ወይስ ጨቅላ?
09/22/2025

ዓለም ከአንድ ሐገር የአዉቶሚክ ሥጋት ወደ ዘጠኝ ሐገራት የኑክሌር ሥጋትና ፍጥጫ ያደገችበት 80 ዓመት የሰላም ዘመን ነበር ማለት ይቻል ይሆን? አንዳድ ጥናቶች እንደጠቆሙት የጋራ ማሕበር ከተመሠረተ ከ1945 ወዲሕ ዓለም ከ300 በላይ ከባድ ጦርነቶችን አስተናግዳለች።በአብዛኞቹ ጦርነቶች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መስራች፣ የዓለም ልዕለ ኃያላን መንግሥታት በቀጥታም በተዘዋዋሪም ተካፍለወል።----ዛሬም ከሱዳን እስከ ጋዛ፣ ከዩክሬን እስከ ኮንጎ ዴምክራቲክ ሪፐብሊክ ዓለም ሰላም የላትም


ማሕደረ ዜና፣ ዝክረ-2017 ዓበይት ፖለቲካዊ ክንዉኖች
09/15/2025

2017 ኤርትራን፣ ሶማሊላንድን፣ ሶማሊያንና ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር አስማማም-አጣላ፣ ቱርክን ለሽምግልና ጋበዘም-ጣልቃ አስገባ፣ከበኒ ሻንጉል ጉሙዝ እስከ አዲስ አበባ ኢትዮጵያዉያንን አስደሰተም-አስከፋ ሰበብ ምክንያቱ ሁለትም-አንድም ነዉ ወደብና ግድብ።ዉኃ።በ2017 የኮሪደር ልማትን አዲስ አበባ ላይ ክፉኛ የተፈተነዉ ጎርፍ ነዉ።-ዉኃ፣ወለጋና ደቡብ ኢትዮጵያ ላይ በትንሹ 10 ሰዎችን የገደለዉ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ላይ ሺዎችን ያፈናቀለዉ፣ ደቡብ ወሎ ዉስጥ የተፈናቃዮችን መጠለያ ጣቢያ ያጠፈዉ ጎርፍ ነዉ-ዉኃ።ሥደተኞችን የበላዉ-ባሕር ነዉ።ዉኃ።


የኦሮሚያ የጸጥታ ኹኔታ እና የአዲሱ ዓመት መባቻ
09/08/2025

ዓመታትን ያስቆጠረው የትጥቅ ትግል አሁንም ድረስ መቋጫ አላገኘም ። አንዴ ውጥረት እያነገሰ ሌላ ጊዜ ረገብ እያለ የቀጠለው የታጣቂዎች እና የመንግስት የጸጥታ አካላት ግጭት ለማህበረሰቡ ሌላ ስጋት ካስከተለ ሰነበተ ። ዕገታ ፤ የዘፈቀደ ግድያ እና ዘረፋ ደግሞ ዋነኞቹ ናቸው ።


የነሐሴ 26 ቀን 2017 ዓ/ም ማሕደረ ዜና
09/01/2025


ማሕደረ ዜና፣የኢትዮጵያ ጉዞ አቅጣጫዉ ይታወቅ ይሆን?
08/25/2025

ኢትዮጵያ ከሉሲ ግኝት እስከ አክሱም ሐዉልቶች፣ ዋልያን ከመሰሉ-እንስሳት እስከ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት፣ከሶፍ ዑመር ዋሻ-እስከ ሐረር ግንብ፣ ከአድዋ እስከ ካራማራ ድል የሚደርሱ የጥንታዊ ሥልጣኔ፣ የተፈጥሮ ፀጋ፣ የጀግንነት ታሪኮች ባለቤት መሆንዋ አያከራክርም።የዚያኑ ያክል የርስበርስ ጦርነት፣ የጎሳ ጥቃትና የፖለቲካ ዉዝግብ ኢትዮጵያን ቁል ዉል እየደፈቋት ነዉ።የድሕነት፣የበሽታና የረሐብ አስከፊነት ከተጠቀሰ የኢትዮጵያዉያን ቁጥር የአሐዞች ማድመቂያ ነዉ።የኑሮ ዉድነት፣ሥራ አጥነት፣የስደተኞች ብዛትና ሞት ከተዘረዘረ ኢትዮጵያና ዜጎችዋን ማለፍ አይቻልም።ሥርዓተ አልበኝነት፣ እገታና ዘረፋም ከኢትዮጵያ «መለያዎች» እየተካተቱ ነዉ


ማሕደረ ዜና፣ የዩክሬን ጦርነት፣የጉባኤ ጋጋታና የዲፕሎማሲዉ ዉጣ ዉረድ
08/18/2025

3 ዓመት ከመንፈቅ።ጦርነቱ አንዳዶች እንደገመቱት ከሁለቱም ወገን በመቶ ሺሕ የሚቆጠር ወታደር አልቆበታል።በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ሠላማዊ ሰዉ ተገድሏል።ቆስሏል።ተፈናቅሏልም።በብዙ መቶ ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሐብት ንብረት ወድሟል።ዩናይትድ ስቴትስ፣ የአዉሮጳ ሕብረትና ብሪታንያ ከመቶ ቢሊዮን ዶላር በላይ ከስክሰዋል።ያሸነፈም፣ የተሸነፈም የለም።የጦርነቱ መሠረታዊ ምክንያት ምንም ሆነ ምን ከግዛት ይገባኛል ያለፈ ሰበብ አልቀረበበትም።ተጨማሪ ሕይወት፣ ሐብትና ንብረት እንዳይጠፋ የዩናይትድ ስቴትሱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ማርኮ ሩቢዮ ባለፈዉ ቅዳሜ አንዳሉት ተፋላሚዎች ሰጥቶ ለመቀበል ፈቃደኛ ሊሆኑ ይገባል።


ማሕደረ ዜና፤ የጋዛ እልቂት፣ የእስራኤል አዲስ ዕቅድና የገጠመዉ ተቃዉሞ
08/11/2025

በእስራኤልና በጠላቶችዋ አፀፋ ጥቃት ምዕራባዊ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ፣ ቤይሩት፣ ሐይፋ፣ ቴሕራን፣ ብዙ ሺሕ ሕዝብ አልቋል።የጋዛ ለብቻዉ ነዉ።የግዛቲቱ የጤና መስሪያ ቤት እንዳስታወቀዉ ከ60ሺሕ በላይ ሕዝብ ተገድሏል።ረሐብ የፈጀዉ ሰዉ ቁጥርም ወደ ሁለት መቶ ተቃርቧል።ሚሊዮኖች ተፈናቅለዋል።እስራኤልም ወደ 800 የሚሆኑ ወታደሮች ተገድለዋባታል።22 ወራት።ከዚሕ ሁሉ እልቂት፣ስደት፣ረሐብ፣ ስቃይ-ሰቆቃ፣ በኋላ የጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ ዕቅድ ከግብ አልደረሰም።


ማሕደረ ዜና፣ ሒሮሺማ-የመጀመሪያዋ የአዉቶሚክ ቦምብ ሰለባ 80ኛ ዓመት
08/04/2025

«ያየነዉን ማመን በጣም ከባድ ነበር።» አሉ ኮሎኔል ቲቤትስ ኋላ።«አንዱ ባልደረባችን «የፈጣሪ ያለሕ» ሲል ሰማሁት» አከሉ ኮሎኔሉ።እነሱ የሚጥበረብር አስደንጋጭ ብልጭታ፣ ሰቅጣጭ-ድምፅ፣ ሐምራዊ፣ሰማያዊ ነጭ ቀለም ያለዉ ወፍራም፣ እምቅ፣ ጢሱን ሰንጥቀዉ ወደ መጡበት ተፈተለኩ።መሬት ላይ ለነበሩት ግን የዕልቂት እቶን በር ተበረገደ።አፍንጫ የሚሰነፍጥ ቅርናት፣ጆሮን የሚሰቀጥጥ የሰቆቃ ጩኸት፣ ከተቀመጡት አስፈንጥሮ የሚያንሳፍፍ ንዝረት፣ ትንፋሽ የሚያሳጣ ወበቅ---ዕልቂት።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ሐሪስ ኤስ ትሩማን እንዳሉት ግን ለዩናይትድ ስቴትስና ለተባባሪዎቿ ታላቅ የታላቅ ድል የመጀመሪያ ምዕራፍ ነዉ


ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ ፈርጀ ብዙ ቀዉስ ማብቂያ ያገኝ ይሆን?
07/28/2025

የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ሥልጣን የያዙ ይሁኑ ተቃዋሚዎች ምንም አሉ-አደ,ረጉ፣ግጭት፣ጥቃት፣ ግድያ፣ እገታ፣ዘረፋና ስርዓተ አልበኝነት ግን ለኢትዮጵያዉያን የአዘቦት ትርዒት እስኪመስል ድረስ እንደቀጠለ ነዉ።የመንግሥት ባለሥልጣናትና ደጋፊዎቻቸዉ የቀዉሱን ንረት፣የሚያደርሰዉን ጥፋትና ምናልባት መፍትሔዉን የሚነግሯቸዉን ሁሉ የዚሕ ወይም የዚያ ጎሳ፣ ቡድንና ፓርቲ አባል እያሉ ከመፈረጅ ባለፍ እስካሁን መፍትሔ መስጠት አልቻሉም።ወይም አልፈለጉም።የኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብታዊ ድቀት፣ ግጭት፣ ጥቃትና ምሥቅልቅሉ ኢትዮጵያዉያን ላይ የሚያደርሰዉ ጥፋት፣ አልበቃ ያለ ይመስል ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሐገራት ጋር የገጠመችዉ አተካራ ሌላ ጭንቀት ሆኗል


ማሕደረ ዜና፣ የቀይ ባሕር አካባቢ መንግሥታት ዉስብስብ ግጭትና ዉጥረት
07/14/2025

ነሐሴ ላይ አዲሱ የሶማሊላንድ ፕሬዝደንት አብዱረሕማን መሐመድ ኢሮ አዲስ አበባን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።ጉብኝቱ «በጠወለገዉ» የመግባቢያ ስምምነት ላይ ነብስ ከዘረባት እስካሁን ገሚስ የህወሓት መሪዎችን የክበቡ አካል ለማድረግ የሚዉተረተረዉ የሞቃዲሾ፣ ካይሮ፣ አሥመራ ገዢዎች አክሲስ ወይም ሥብስብ ምናልባት የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦብነግ) ገሚስ መሪዎችን ሊያቅፍ፣ አጓጉል መዘዙ ከትግራይ እስከ ኦጋዴን ሊደርስ ይችላል።


ማሕደረ ዜና፣ የጋዛ ተኩስ አቁም ተስፋ፣ የመካከለኛዉ ምሥራቅ ዕዉነታ
07/07/2025

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቢኒያሚን ኔታንያሁ ዛሬ ዋሽግተን ዉስጥ ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በሚያደርጉት ዉይይት ሁለቱ መሪዎች የዓመት ከዘጠኝ ወራቱን ወታደራዊ ዘመቻ ለ60 ቀናት ለማቆም ያላቸዉን ዕቅድ ያስታዉቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።ዩናይትድ ስቴትስና ቀጠር አቀረቡት የተባለዉን ሐሳብ እስራኤልም-ሐማስም ተቀብለዉታል ተብሏል።ሐሳቡ መፅደቅ-መዉደቁ የሚወሰነዉ ግን በትራምፕና በኔትንያሁ ትዕዛዝ ነዉ።


ማሕደረ ዜና፤ የእስራኤል፣ የአሜሪካና የኢራን የጦርነት ማግሥት የጦርነት ዝግጅት
06/30/2025

በርግጥ ጀግናዉ ማነዉ? 12 ቀናት የቆየዉን፣ከ600 በላይ ኢራናዉያንን፣ 28 እስራኤላዉያንን የገደለዉን፣ የሁለቱን ሐገራት ምጣኔ ሐብት ያሽመደ።መደዉን ዉጊያ ቀድማ የከፈተችዉ እስራኤል ናት።ዩናይትድ ድብደባዉን ፈቅዳለች፣ ኋላ ራሷ ቀጠላበታለች።አሁን የሚሞጋገሱት የሁለቱ ጥብቅ ወዳጅ መንግሥታት መሪዎች ኢራንን ለመደብደባቸዉ የሰጡት ምክንያት የቴሕራንን የኑክሌር ተቋማት ለማዉደም ነዉ።ወሕኒ ቤት የኑክሌር ተቋም ይሆን?


ማሕደረ ዜና፤ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ዉጊያ፣ መዘዙና ሕግ አልባዋ ዓለም
06/23/2025

የቀድሞዉ የዶናልድ ትራምፕ የፀጥታ አማካሪ ጆን ቦልተን ባንድ ወቅት «የዓለም ማሕበረሰብ የሚባል ነገር የለም።ያለችዉ አንድ ልዕለ ኃያል ሐገር ናት-ዩናይትድ ስቴትስ።» ብለዉ ነበር።አላበሉም።ዓለም የጋራ ማሕበር፣ ፍርድ ቤት፣ ሕግ፣ ደንብ፣ ሥምምነት የሚኖራት ለአሜሪካና ለእስራኤል እስከጠቀመ ብቻ ነዉ።ባይሆን ኖሮ ሩሲያ ዩክሬንን መዉረሯ ከተወገዘ፣ በማዕቀብ ካስቀጣ፣እስራኤልና አሜሪካ ሊባኖስን፣የመንን፣ ሶሪያን፣ኢራንን መደብደባቸዉ፣ታጣቂዎችን ከሕሙማን ሳይለዩ መግደላቸው የማያስወገዝ፣ የማያስጠይቅ፣ የማያስቀጣበት ምክንያት የለም።


የእስራኤል ኢራን ጦርነት ዓለማቀፍ ስጋት ደቅኗል
06/17/2025


የእስራኤል ኢራን ግጭት እና የደቀነው ብርቱ ስጋት
06/16/2025

ያ የተፈራው ፤ ያ እንዳይመጣ የተሰጋው ቀንና ሰዓት ደረሰ። ለአራት አስርት ዓመታት የዘለቀው የከፋ ጠላትነት ገነፈለ ፤ በመጨረሻም እስራኤል ክብሪቱን ለኮሰች ፤ የኢራን እስራኤል የአየር ላይ ጦርነት የእሳት ኳስ እያወራወረ አራተኛውን ቀን አስቆጠረ ፤ ሀገራቱ በታሪካቸው አይተው ያማያውቁትን ውድመት እና የሰብአዊ ቀውስ እያስተናገዱ ነው ።


ማሕደረ ዜና፤ ሊቢያ፣ ኃያላን ያወደሟት፣ታጣቂዎች የሚተራመሱ፣ ዘራፊዎች የሚሻሙባት ሐገር
06/02/2025

የአሜሪካዉ ዜና አገልግሎት አሶስየትድ ፕሬስ በ2022 እንደዘገበዉ በፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ዉሳኔ የዘመተዉ የኔቶ ጦር ከመርከብ የተኮሰዉ ሳይቆጠር በጦር ጄት ብቻ ሊቢያን 10ሺሕ ጊዜ ደብድቧል።በድብደባዉ የተገደለዉን ሰዉ ቁጥር እስከ 500,000 የሚያደርሱት አሉ።መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ግን የተገደሉት ሰላማዊ ሰዎች ቁጥርን ሲያንስ 70 ሲበዛ 403 ያደርሱታል።የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ምብቶች ምክር ቤት የኔቶ ጦር 60 ሰላማዊ ሰዎች መግደሉን አረጋግጧል።ሟች ቁስለኛዉ 60፣70፣400 ይሁን 500 መቶ ሺሕ ተጠያቂዎች ለፍርድ ቀርበዉ ይሆን? ሐገር ማፍረስስ ያስወነጅል ይሆን? አናዉቅም።ሊቢያ ግን በርግጥ ፈርሳለች።


የፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትችትና ነቀፋ የዳግም ጦርነት ዝግጅት ይሆን?
05/26/2025

ፐሬዝደንት ኢሳያስ እንደሚሉት ኢትዮጵያ ዉስጥ ወይም ባካባቢዉ የታወጀ ጦርነት አንድ አይደለም። «ብዙ ጦርነቶችን ለማስቀጠል ዘመናይ ቴክኖሎጂና ጦር መሳሪያ እየተሰበሰበ ነዉ» ብለዋል።የብልፅግና ፓርቲ ለቴክኖሎጂና ለጦር መሳሪያ የሚያወጣዉ ዶላርም ልክ የለዉም ብለዋል።ኢሳያስ «ርካሽ» ያሉት ፉከራና ቀረርቶ በእሳቸወ አገላለፅ ተመዝግቧል።«የኤርትራን ሕዝብና መንግሥትን ወደ ግጭት ለማስገባት የሚሸረበዉ ግልፅና ሥዉር ሴራን ያላወቀዉ የለም» ይላሉ የኤርትራዉ ፕሬዝደንት።የዳግም ጦርነት ዝግጅት ይሆን?


ማሕደረ ዜና፣ የምርጫ 97 ሒደት፣ዉጤትና አሳዛኝ ፍፃሜዉ 20 ዓመት ደፈነ
05/19/2025

ከ25 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምፅ ሰጥቶበታል።ሕዝባዊ፣ ታሪካዊ፣ አብነታዊም ነበር።የአሸናፊ-ተሸናፊዉ ዉዝግብ፣ የገዢዉ ፓርቲ ጨካኝ ርምጃና እስከዛሬ የተረፈዉ መዘዝ ሲጤን ግን ራቅ ሲል በ1953 በአፄ ኃይለ ሥላሴ ላይ ከሞከረዉ መፈንቅለ መንግስት፣ ቀረብ ሲል በ1969 በኮሌኔል መንሥቱ ላይ ከተሞከረዉ የግድያ ጥቃት ዉጤት ጋር የሚያመሳስሉት አሉ።


ማሕደረ ዜና፣ ሕንድና ፓኪስታን የዝንተ ዓለም ጠላቶች
05/12/2025

የሒንዱ፣የሲክና የቡዳሐ አማኞች በብዛት የሚኖሩበት ግዛት ሕንድ ሲባል፣ ሙስሊሞች የሚበዙበት የዛሬዎቹ ፓኪስታንና ባንግላዴሽ ግዛቶች ደግሞ ፓኪስታን ሆኑ።ክፍፍሉ ሲደረግ ሙስሊሞች በብዛት የሚኖሩበት የጃሙ ካሽሚር ካሽሚር ግዛት ግን የሒንዱ እምነት የሚከተሉት የግዛቱ አገረ-ገዢ እንደጠየቁት ነፃ መንግስትም ሳይሆን፣ ከፓኪስታንና ሕንድም ሳይጠቃለል ለወደፊቱ ግጭት እንዲመች ተንጠልጥሎ ቀረ።


ማሕደረ ዜና፣ የፕሬዝደንት ትራምፕ ሠላም የማስፈን ቃልና ተቃራኒ ርምጃ
05/05/2025

በሳምንቱ መገባደጃ ላይ ደግሞ የእስራኤል ጦር ገና በቅጡ ያልጠናዉን የሶሪያ መንግስት ይዞታዎችን በተዋጊ ጄቶች ደብድቧል።እስራኤል ጋዛን፣ ምዕራባዊ ዮርዳኖስ ዳርቻን ፣የመንን፣ ኢራንን፣ ሊባኖስን መናደፏ አልበቃ ብሏት በተለያዩ የሶሪያ ጎሳ ወይም የሐይማኖት ሐራጥቃ ተከታዮች መካከል በተነሳ ጠብ ጣልቃ ገብታ በ14 ዓመት ጦርነት የወደመችዉን ሶሪያን ደጋግማ መደብደቧ ለብዙ ታዛቢ ግራ አጋቢ ነዉ።ሶሪያዊ አዛዉንት እንደሚሉት ግን የእስራኤል ጥቃት በአረብ መሪዎች ዝምታ፤ በዶንልድ ትራምፕ ይሁንታ የታገዘ ነዉ።


ማሕደረ ዜና፣ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ቃል፣ መርሕና እርምጃ ቁንፅል ትዉስታ
04/28/2025

ሕይወቱን ለኃይማኖት ከሰጠ በኋላ ግን እንደ ድሆች ሁሉ ለስደተኞችም ሲሟገት አድጎ፣ጦርነትን ሲቃወም በስሎ አርጅተዋል። ፍራንሲስ። በ 12 ዓመታት የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሥልጣናቸዉ ዘመን 68 ሐገራትንና በመቶ የሚቆጠሩ ግዛቶችን ጎብኝተዋል።ከሮም ዉጪ መጀመሪያ የጎበኙት ግን በአብዛኛዉ የአፍሪቃ ስደተኞችን የሜድትራንያንን ባሕር ለማቆረጥ ሲቀዝፉ በብዛት የሚልቁበትን ባሕር፣ ከዳኑ የሚያርፉበትን ደሴት ነበር።ላፔዱዛን ሐምሌ 8፣ 2013


ማሕደረ ዜና፣የሱዳን ዉድመትና የመከፋፈሏ ሥጋት
04/21/2025

ያለመግባባቱ ምክንያቶች ከሩቅ ያሉት በቅኝ ገዢነት ብዙ ጊዜ የሚወቀሱት አዉሮጶች፣ በአረብ ጠላትነት የምትወገዘዉ እስራኤል ወይም አሜሪካኖች አይደሉም።የሱዳንን ሕዝብ «ወንድም» የሚሉት፣ከአብዛኛዉን ሱዳናዊ ጋር ቋንቋ፣ ባሕል፣ ኃይማኖት የሚጋሩት አረቦች እንጂ።ሳዑዲ አረቢያ፣ ግብፅና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በጋራ መግለጫዉ ይዘት ላይ አልተስማሙም።


ማሕደረ ዜና፣የሱዳን ዉድመትና የመከፋፈሏ ሥጋት
04/21/2025

የለንደኑ ጉባኤ የተደረገዉ ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ ያደረጁት «የሱዳን የሰላምና የአንድነት» ወይም የሱዳን ትዩዩ መንግሥት መመሥረቱ ናይሮቢ ላይ በታወጀ ማግሥት፣አል ቡርሐን የሚመሩት መንግስት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን በዘር ማጥፋት ወንጀል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፍርድ ቤት ላይ በከሰሰ ሳልስት ነበር።ሚዚያ 16።ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ የሚመሯቸዉ ቡድናት በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የገንዘብ ድጋፍ፣በኬንያዉ ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ አስተናጋጅነት የትይዩ መንግስት መመሥረታቸዉን ግብፅና ሳዑዲ አረቢያ አዉግዘዉታል


ማሕደረ ዜና፣ የኢራን-አሜሪካ ድርድር ጠብ-ግጭቱን ያበርድ ይሆን?
04/14/2025

የሙጃህዲያን ኢ-ኻሊቅ (MEK)ና የቡድኑ ምክር ቤት መሪዎች ኢራን በ1967 ከአሜሪካ ባገኘችዉ ድጋፍ የጀመረችዉን የኑክሌር መርሐ ግብርን ወደ ኑክሌር ቦምብ መስሪያነት ለመቀየር ናታንዝና አራክ ዉስጥ በድብቅ እያብላላች መሆኑን ለዓለም አረዱ።ወይም አበሰሩ።ነሐሴ 2003።ዋሽግተን።ሲሞን ሔርሽና ኮኒ ብሩክ የተባሉት መርማሪ ጋዜጠኞች እንደፀፋት የሙጃህዲያን ኢ-ኻሊቅ መሪዎች የቴሕራኖችን ሚስጥር እንዲያጋልጡ የገፋፏችዉ መረጃዉንም የሰጧቸዉ የእስራኤል ባለሥልጣናት ናቸዉ።


ማሕደረ ዜና፣ የአሜሪካና የኢራን ፍጥጫ-የመካከለኛዉ ምሥራቅ ምሥቅልቅል ሌላ ገፅታ
04/07/2025

የቴሕራን የፖለቲካና የጦር ሹማምንት ደግሞ ለፕሬዝደንት ትራምፕ ዛቻ አፀፋ ዛቻ እየሰነዘሩ ነዉ።የአያቶላሕ ዓሊ ኻማኒይ የቅርብ አማካሪ አሊ ላርጃኒ ባለፈዉ ሳምንት እንዳሉት ኢራን የኑክሌር ቦምብ መታጠቅ አትፈልግም።የአሜሪካኖች ዛቻ ከበረታ ግን ቀጠሉ የቀድሞዉ የኢራን የኑክሌር ጉዳይ ተደራዳሪ «ሌላ ምርጫ የለንም---መታጠቅ እንጂ።»


ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ ፈርጀ ብዙ ቀዉስ
03/31/2025

የብርቱካን ተመስገን ትረካ እዉነት-ሐሰትነት ለብዙዎች በጣሙን እሁለት ለተገመሱት ለማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ አስተያየት ሰጪ-ተከታታዮች ማከራከሩን እንደቀጠለ ነበር።ግን እንዲያዉ ለመጠየቅ ያሕል 120 ሚሊዮን የሚሆነዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሐቁን የሚያወጣ አንድ መርማሪ ፖሊስ፣ አንድ መርማሪ የሕግ ባለሙያ፣ አንድ መርማሪ ጋዜጠኛ፣ አንድ የምክር ቤት አጣሪ ኮሚቴ እንዴት አጣ?


ማሕደረ ዜና፣ ሱዳኖች አንድም ሁለትም ሆነዉ ከግጭት-ጦርነት ያልተዩ ሐገራት
03/24/2025

የማቻር ደጋፊ የሚባሉት የኑዌር ጉሳ ሚሊሻዎች ኢትዮጵያን በሚያዋስነዉ ድንበር አካባቢ ከሠፈረዉ ከፕሬዝደንት ሳልቫኪር መንግስት ጦር ጋር መዋጋት ከጀመሩ ሳምንት አልፈዋል።የጁባዎች ጠብ የናረዉ ጁባዎች ከጋራንግ ሞት በኋላ እንዳደረጉት ሁሉ ከአል በሽር መወገድ በኋላ ዋና እና ምክትል ሆነዉ የካርቱም ሪፐብሊካን ቤተ መንግስትን የተቆጣጠሩት የሱዳን ጄኔራሎች የገጠሙት ጠብ በጦር ሜዳዉም በፖለቲካዉም መስክ ወደ አዲስ ምዕራፍ በተሸጋገረበት ወቅት መሆኑ ነዉ።የፈጥኖ ደራሹ ጦር ከደቡብ ሱዳን ቡድናት ካንደኛዉ ጋር ያለዉን ትብብር ከማጠናከርም አልፎ የትይይዩ መንግስት--- ዳርፉር ግዛት ሊመሰርት ይችላል የሚለዉ ግምትም እያየለ ነዉ


“መፈንቅለ-መንግሥት” ወይስ “ሕግ ማስከበር” የትግራይ ቅርቃር
03/17/2025

የህወሓት አመራሮች ልዩነት ሲበረታ በደም አፋሳሽ ጦርነት ውስጥ ያለፈው የትግራይ ክልል ነዋሪ “ነገስ ምን ይፈጠራል?” በሚል “እየተሳቀቀ እንዲኖር” ተገዷል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ጦርነት ይቀሰቀሳል በሚል ሥጋት “ሰዉ በጣም ተረባብሿል”፤ በኅብረተሰቡ ዘንድ “መከፋፈል” ተፈጥሯል። ነጋዴዎች የዋጋ ጭማሪ በማድረጋቸው “የኑሮ ውድነቱ እያሻቀበ” ነው።


ደቡብ ሱዳን ወደ የርስ በርስ ጦርነት ዳግም እየተንሸራተተች ይሆን?
03/10/2025

ከኢትዮጵያ ድንበር 30 ኪሎ ሜትር በምትርቀው ናስር ከተማ በደቡብ ሱዳን ጦር ሠፈር ላይ የተፈጸመ ጥቃት ጁባን ፖለቲካዊ ውጥረት ውስጥ ከቷታል። በናስር በሚገኝ የደቡብ ሱዳን የጦር ሠፈር ላይ ባለፈው ሣምንት ጥቃት የፈጸመው ዋይት አርሚ ተብሎ የሚጠራ የኑዌር ጎሳ ታጣቂ ቡድን ነው። ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር ምክትላቸው ሪየክ ማቻርን ሳያማክሩ የወሰዷቸው ርምጃዎችም ቅሬታ ፈጥረዋል። ሁለቱ የተፈራረሙት የሰላም ሥምምነት ፈርሶ ደቡብ ሱዳን ወደ የርስ በርስ ጦርነት እንዳትገባ ሥጋት አለ።