ስፖርት | Deutsche Welle
የሚያዝያ 27 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
የፕሬሚየር ሊጉን ዋንጫ መውሰዱን ገና አራት ጨዋታዎች እየቀረው አረጋግጦ የነበረው ሊቨርፑል ትናንት በቸልሲ ብርቱ ሽንፈት ገጥሞታል ። በጀርመን ቡንደስሊጋ ቅዳሜ ዕለት ከኤርቤ ላይፕትሲሽ ጋር ሦስት እኩል የተለያየው ባዬርን ሙይንሽን ሁለት ጨዋታዎች እየቀሩት ዋንጫውን መውሰዱን አረጋግጧል ። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለድል በቅተዋል ።
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ
የሚያዝያ 20 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
ሊቨርፑል የፕሬሚየር ሊጉን ዋንጫ መውሰዱን ገና አራት ጨዋታዎች እየቀሩት አረጋግጧል ። ባርሴሎና ደግሞ የኮፓ ዴል ሬይ ዋንጫን ከሪያል ማድሪድ ጋር አንገት ለአንገት ተናንቆ መንትፏል ። በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲንየም ደረጃ በተሰጠው የለንደን ማራቶን የሩጫ ፉክክር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትእግስት አሰፋ ክብረ-ወሰን በመስበር ጭምር አሸናፊ ሁናለች ።
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ
ስለ አደንዛዥ እጽ ሱሰኝነትን ወጣቱ ምን ይላል?
ለመሆኑ የአደንዛዥ እጽ እና ሌሎች ሱስ አስያዥ ነገሮች ወጣቱ ላይ ምን ተጽእኖ ያሳርፋሉ እንዴትስ መታገል ይቻላል? በሜክሲኮ ወጣቶችን ከሱስ ለማላቀቅ በሚል በሺህዎች የሚቆጠሩ አብዛኛ ወጣቶች የታደሙበት የአደባባይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተደርጓል ። በኢትዮጵያስ ወጣቶች ምን ይላሉ?
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ
የመጋቢት 22 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
ሐዋሳ ከተማ ውስጥ በተከናወነው የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ግጥሚያ የግማሽ ፍጻሜ አላፊዎች ተለይተዋል ። በእንግሊዝ ኤፍ ኤካፕም እንደዛው ። ናይጄሪያዊው ቡጢኛ ጋና ውስጥ የቡጢ መፋለሚያ መድረክ ላይ በአሳዛኝ ሁኔታ ሕይወቱ አልፋለች ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን አንዳንድ ተጨዋቾች የስነምግባር ጉዳይ አነጋግሯል ።
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ
የመጋቢት 15 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
በቻይና ናንጂንግ የዓለም የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ፉክክር ኢትዮጵያ ዩናይትድ በ3ተኛ ደረጃ አጠናቃለች ። በግብጽ የ2 ለ0 ሽንፈት ያስተናገደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከጅቡቲ ጋር ዛሬ ማታ ይጋጠማል ። በአውሮጳ የኔሽንስ ሊግ ጀርመን ከፖርቹጋል ሙይንሽን አሬና ውስጥ፤ ስፔን ከፈረንሳይ ጋር ደግሞ ሽቱትጋርት አሬና ውስጥ ይጋጠማሉ ።
የመጋቢት 8 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
በደቡብ ኮሪያ የሴዑል ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንድም በሴትም አሸናፊ ሁነዋል ። በባርሴሎና ማራቶንም ድል ተገኝቷል ። በእንግሊዝ የካራባዎ ዋንጫ የፍጻሜ ግጥሚያ ኒውካስትል ትናንት በአሌክሳንደር ኢሳቅ ወሳኝ ግብ ሊቨርፑልን አሸንፏል ። አርሰናል በለንደን ደርቢ ቸልሲን አሸንፏል ። ላይፕትሲሽ ዶርትሙንድን 2 ለ0 ኩም አድርጓል ።
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ
የመጋቢት 01 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
ቻይና የምታሰናዳው የናንጂንግ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ፉክክር በተቃረበበት በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ውዝግብ ተከስቷል ። ቃለ መጠይቅ አድርገናል ። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ሊቨርፑል የዘንድሮ ዋንጫን ለማንሳት ከወዲሁ ዳር ዳር እያለ ይመስላል፥ በሳምንቱ መጨረሻ አስተማማኝድ ድል ሲቀዳጅ ተከታዩ አርሰናል ዳግም ነጥብ ጥሏል ።
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ
የየካቲት 24 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
በጃፓን ቶኪዮ ማራቶን እንደተጠበቀው ሁሉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በወንድም በሴትም ፉክክር አሸንፈዋል ። ሉሲዎቹ በመለያ ምት ዩጋንዳን አሸንፈው ወደ ቀጣዩ ሁለተኛ ዙር አልፈዋል ። በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ አምስተኛ ዙር የእግር ኳስ ግጥሚያ ዛሬ ማታም ይኖራል ። ባየርን ሙይንሽን በአሸናፊነቱ እየገሰገሰ ነው ።
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ
የየካቲት 17 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የማራቶን ውድድሮች በወንድም በሴትም ፉክክር ድል ተቀዳጅተዋል። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ሊቨርፑል በግስጋሴው ቀጥሎ በ11 ነጥብ ልዩነት ተከታዩ አርሰናልን ርቋል ። በመጀመሪያው ግጥሚያ በውድድሩ ማብቂያ ላይ በዩጋንዳ አቻቸው የተሸነፉት ሉሲዎቹ በመልሱ ግጥሚያ ረቡዕ ይፋለማሉ ።
የየካቲት 17 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
የየካቲት 10 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
በፖላንድ ኦርሌን የዓለም የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለድል በቅተዋል ። በ800 ሜትር ውድድር አትሌት ፅጌ ዱጉማ 2:00.04 በመግባት በአንደኝነት አጠናቃለች ። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ መሪው ሊቨርፑልን ዎልቭፍስ እጅግ ፈትኖታል ። የማንቸስተር ሲቲው ዖማር ማርሙሽ በ19 ደቂቃዎች ውስጥ 3 ግቦችን በማስቆጠር ሔትትሪክ ሠርቷል ።
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ
የየካቲት 3 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የዓለም መድረኮች ድል ቀንቷቸዋል ። በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ ግጥሚያ፦ ፕሌይማውዝ አርጊል በአስደንጋጭ ሁኔታ ሊቨርፑልን 1 ለ0 በማሸነፍ ከአራተኛ ዙር ውድድር አሰናብቶታል ። በስፔን ላሊጋ በዐሥር ተጨዋቾች የተወሰነው ባርሳ ተጋጣሚው ሴቪያን በሰፋ የግብ ልዩነት 4 ለ1 አሸንፏል ።
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ
የጥር 26 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
የዩጋንዳ አቻቸውን ለአፍሪቃ ዋንጫ ማጣሪያ የሚገጥሙት ሉሲዎቹ ከጅቡቲ ጋር የወዳጅነት ግጥሚያ ሊያደርጉ ነው ። ጅቡቲ በበርካታ ቡድኖች በርካታ ግብ አስተናግዶ አንድም ሳያስቆጥር የሚሸኝ ነው ። ቃለ መጠይቅ ይኖረናል ። የእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ እና የጀርመን ቡንደስሊጋ ውጤቶችንም አጠር አድርገን እናቀርባለን ።
ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዲሱ ፕሬዚደንት ምን ይጠበቃል? አንድ ለአንድ፥ ቃለ መጠይቅ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽ የአገራቸውን ስም በዓለም መድረክ ያስጠሩ በርካታ ብቃት ያላቸውን አትሌቶች ፌዴሬሽኑ የማፍራቱን ያህል በተለያዩ አወዛጋቢ ጉዳዮችም ስሙ በተደጋጋሚ ይነሳል ። ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዲሱ ፕሬዚደንት አትሌት ስለሺ ሥኅን ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ ። ሙሉ ቃለ መጠይቁን በድምፅ ማእቀፉ ማድመጥ ይቻላል ።
የጥር 19 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
እንደተለመደው ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዓለም የውድድር መድረኮች ድል ቀንቷቸዋል ። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ፉክክር አርሰናል ወሳኝ የሆነ ድሉን በአንዲት ብቸኛ ግብ አግኝቷል ። ሊቨርፑል በመሪነቱ እንደገሰገሰ ነው ።
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ
የጥር 12 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዩናይትድ ስቴትስ ሒውስተን ውስጥ በተከናወነው የግማሽ ማራቶን የሩጫ ፉክክር በወንዶችም በሴቶችም አሸንፈዋል ። ቃለ መጠይቅ ይኖረናል ። በማራቶንም ድል ቀንቷቸዋል ። ፉክክሩ በተጧጧፈበት የእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው መሪው ሊቨርፑል ተከታዩ አርሰናልን በስድስት ነጥብ ርቆታል ።
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ
የታኅሣሥ 28 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች እንደተለመደው በሳምንቱ መጨረሺያ ላይ በዓለም አቀፍ ውድድሮች ድል ተቀዳጅተዋል ። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ በደረጃ ሰንጠረዡ ቁልቁል ላይ የሚገኘው ማንቸስተር ዩናይትድ የምንጊዜም ተቀናቃኙ ሊቨርፑል ላይ ትናንት በርትቶ ታይቷል ። አርሰናል ከመሪው ሊቨርፑል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ማጥበብ የሚችልበትን አጋጣሚ አምክኗል ።
የታህሳስ 21 ቀን 2017 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅት
አትሌቲክስ ስፖርት እና የእግር ኳስ ዘገባዎች
28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መረጠ ። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን በመተካት ለቀጣይ 4 አመት ፌዴሬሽኑን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ሰህንን መምረጡ ይታወሳል።
የሰኞ ታኅሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም. የስፖርት ዝግጅት
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን የጠቅላላ ጉባኤ ምርጫ በመጨረሻም ታዋቂውን አትሌት ስለሺ ስህንን አዲሱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል። በጀርመን ማግድቡርግ መሀል ከተማ በሚገኝ የገና ገበያ ላይ የተፈጸመ ጥቃት የቡንደስሊጋ የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ የሀዘን ድባብ ፈጥሯል።
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ
የታኅሣሥ 7 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
በኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት ምርጫ ውዝግቡ ቀጥሏል ። በዛሬው ስብሰባ ምን ተከሰተ? ቃለ መጠይቅ አድርገናል ። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ በ10 ተጨዋቾች የተጋጠመው መሪው ሊቨርፑል ነጥብ ተጋርቷል ። ማንቸስተር ሲቲ በማንቸስተር ዩናይትድ ተሸንፏል ። አርሰናል ነጥብ ጥሏል ። ዝርዝሩን ከዘገባው ።
የኅዳር 30 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች 26,000 ሯጮች በተሳተፉበት የጉዋንጁ ማራቶን ክብረወሰን በመስበር ድል ተቀዳጅተዋል ። በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ የአርሰናል እና የማንቸስተር ሲቲ ነጥብ መጣል ለቸልሲ መልካም አጋጣሚ ሁኗል ። ቀሪ ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው ሊቨርፑልን በ4 ነጥብ ተጠግቷል ።
ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ
የኅዳር 23 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዓለም መድረክ ምርጥ ተብለው ተመርጠዋል፤ ለድልም በቅተዋል ። ግብጻውያን የእግር ኳስ አጥቂዎች በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ እና ጀርመን ቡንደስ ሊጋ ገንነዋል ። ሊቨርፑል ከዋነኛ ተቀናቃኞቹ አንዱ ያለፈው የውድድር ዘመን ዋንጫ ባለድሉ ማንቸስተር ሲቲን ትናንት ጉድ አድርጓል ።